Home

ርዕየ-አዳራሽ
ሃገርን ከጥፋት የመታደግ ጥሪ

፩. የወቅትዑ የኅልውና አደጋ
ጥንትዓዊትዋ፣ ታሪክዓዊትዋ እና ታላቅዒትዋ ኢትዮጵያችን፤ የ ኅልውና አደጋ ላይ ነች። ጀግናዉ እና ቅንዑ ህብረ-ማኅበረሰብዐችን — ወረራ፣ ዝርፊያ እና የ ኅልውና አደጋ ተጋርጦበት አ። የ ኅልውና አደጋዉ ትልም የተወጠነዉ፤ ጥንት፡ በ ባዕዳን ምሆንዑ ዕሙን ነው። ባዕዳንዑ፤ ጊዜያዊ ጥቃት እና ጉዳት ከማስከተልዐቸዉ ባ’ፈ፡ ዘላቂዕነት ባ’ዉ መልክዑ ትልምዐቸዉን ተግባርዓዊ ማድረግ ሳይችሉ ቢቀሩም ቅሉ — ኢትዮጵያችን፡ ጥቂት የራስዋ ጠማማዎች፡ የባዕዳንዑን ትልም ፍፃሜ ላይ ሊይአደርሱላቸዉ፡ ሃገርዐችንን እና ህብረ-ማኅበረሰብዐችንን፡ የ ከ የ ኅልውና አደጋ ውስጥ እንድይዘፈቅዑ ምክንያት ሆነዉዐል።

፪. የውስጥ ባንዳዎች እና የስርዐትዑ ችግር
የ ኅልውና አደጋዉን ልዩ እምይአደርገዉ፤ አብልታ፣ አጠጥታ ባ’ሳደገችዐቸዉ፡ በ የውስጥ ባንዳዎች እይኧተተገበረ ያ’ ከ ምሆንዑም ባ’ሻገር — የ መንግሥት ሥልጣንን፣ የ-መንግሥት መዋቅርዐትን እና የ ሃገሪትዋን [የ ራስዋን] ዕሴትዖች ተቆጣጥረዉ እምይፈፅሙት የግፍ-ግፍ የምሆንዑ መራር ዕውነትዐ ነው። ትክክል። ዛሬ በስራ ላይ እይኧዋለ ያዉ፤ በጎሳ፣ በ ቋንቋ እና በ ጎጥ ላይ የተመሠረተዉ ፌደራሊዝም፡ እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ህብረ-ማኅበረሰብ፡ ለ የተዘፈቅንበት የ ኅልውና አደጋ፡ መሠረትዓዊ ምክንያት ነው።

፫. መፍትሄዉ፦ ስር‑ነቀል ለውጥ
መፍትሄው፤ ግልፅ ነው። ኢትዮጵያዊ ሕዝብዓዊ ኃይል በማደራጀት እና ሁልኧገብ ህብረ-ማኅበረሰብዓዊ እንቅስቃሴን በማቀጣጠል፤ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማፅናት፣ ለማስቀጠል እና ለማዘመን እምይአስችል ስር-ነቀል የ ስርዐት ለዉጥ ማምጣት ብቻ ነው።

ሀ.  ቅንጅት የ ኢትዮጵያ ሕዝብን፣ የኢትዮጵያ የፖሊቲካ አደረጃጀትዖችን፣ የ ኢትዮጵያ ሙያ‑ማኅበርዐትን እና የ ኢትዮጵያ የሲቪክ ድርጅትዖችን ጥምረት ማቀናጀት።
ለ.  የሽግግር መንግሥት ኢትዮጵያዊ ሕዝብዓዊ የሽግግር መንግሥት፡ እምይፈጠርበትን ሂደት፡ በ ቁርጥኧኛዕነት እና በቅንዕነት ዛሬዉንዑ መጀመር።
ሐ.  ማስጠንቀቂያፀረ‑ኢትዮጵያ እና ፀረ‑ኢትዮጵያዊነት የሆነ አቋም እና ተቋም የነበራቸዉ እና ያቸው አደረጃጀቶች ተነቅሰው፤ ተጠይዐቂነትን ባግባቡ ለመተግበር፡ የፈፀሙት እና እየፈፀሙት ያዉ የኅልውና አደጋ እንድያከትም፣ እንደገና እንድአይከሰት እና ሙሉ‑በ‑ሙሉ እንድይቀለበስ ለማድረግ፡ የተፈፀሙት ወንጀሎች፣ ሃጥያቶች እና ነውሮች፡ ሳይዉል ሳይአድር፡ ዛሬውኑ፡ ህግ ፊት እና ሕዝብ ፊት እንድይቀርቡ ማድረግ፡ ሊነጋ እምአይባ  የትውልድ አደራ ተደርጎ መወሰድ አለበት።

፬. የመጪዉ ዘመን ተስፋ
ኢትዮጵያችን፤ ኢትዮጵያዊ መንግሥትም ሆነ ኢትዮጵያዊ ህገ‑መንግሥት ይኖርዐት ዘንድም — ሃገር አፍራሽ፡ ማለትም — ተገንጣይ ድርጅትዖችን እምአይአካትት፡ ኢትዮጵያዊ ሕዝብዓዊ የ-ሽግግር መንግሥት የመፍጠር ሂደት፡ ዛሬዉንዑ ይጀመር።

የ እምእንእጠብቀዉ የሽግግር መንግሥት፦

ሀ. ዳር‑ድንበርዐችንን ያስከብር፣ ሰላም እና መረጋጋትን ያስፍን።
ለ. የ ሁሉንም ተቋምዐት ተግባርዐት፡ በ ሃላፊዕነት ይምራ።
ሐ. የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ቆጠራ እና ተከትሎ መደረግ ያ’በትን ምርጫ፡ ፍትህዓዊ እና ነፃ መሆኑን ለ ማርኧጋገጥ እምይአስችሉ፡ ተቋምዓዊ ለውጥዖችን ተግባርዓዊ ያድርግ።
መ. ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ ያ’ተፈ፤ አዲስ ስልጡን ህገመንግሥት ይቅረፅ። በ ቋንቋ እና በ ጎጥ ላይ የተመሠረተዉን ፌደራሊዝም፤ ሙሉ‑በ‑ሙሉ እንድይፈርስ ያ’ድርግ። በምትክዑም፤ ሕዝብ እምይመርጠዉን ያ’ስተዳደር ስርዐት እንዲረጋ እምይአስችል ድልዳል ያ’ት። ሰው በሰውዕነትዑ ብቻ እምይከበርበትን፤ በ ዜጋዕነት ላይ ያ’ተኮረ እና የቡድን ጥይዐቄዎችን ያ’ገናዘበ መርህን እምይከተል፣ በ ዲሞክራሲያዊ እና ነፃ ምርጫ፡ ሃገርን የመጠበቅ እና ሕዝብን የማገልገል ዕድልዑን እምይአገኝ — ኢትዮጵያዊ ሕዝብዓዊ መንግሥት ይሥረት።

እናም፤ ኢትዮጵያ ሰላም ታ’ግኝ።

አዳራሽ
ሚያዝያ ፲፰ ቀን፡ ፳፻፲፰ ዓ.ም.


ሉዓላዊ ፈቃድ | የ አዳራሽ ጦማር – ግንቦት ፳፻፲፰ ዓ.ም.

The Sovereign Will | The Adarash Blog, May 2026 G.C.

የሉዓላዊ እምቢታ ዓለም አቀፍ ድምፅ | የ አዳራሽ ጦማር – ግንቦት ፯ ቀን፡ ፳፻፲፰ ዓ.ም.

A Global Mandate for Refusal | The Adarash Blog, May 15, 2026 G.C.