ሕዝብዓዊ እንቅስቃሴ – ዐማራዊ ቅኔ

ሕዝብዓዊ እንቅስቃሴ — ዐማራዊ ቅኔ

የ አዳራሽ ጦማር | መስከረም ፳፻፲፮ ዓ.ም

ትኩረትዐችን፦ በቅድሚያ፤ አዲስ ዓመትን – ከ ዐማራ ማኅበረሰብዐችን ጐን፡ ከ [ፋኖ] ጐን በ መለፍ፡ እንዴት የ’ ድርሻችንን መጣት እንዳብን፡ በ’ ቤትዐችን በ–መምከር እና በ–መመካከር፡ እንኣሳልፍ ዘንድ ባ’ክብሮት ዕየጠየቅን – እንኳን ከ ዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፡ አሸጋገርዐችሁ፡ አሸጋገርኧን፡ ዕ’ንል አን።

በ ማስከተልም፤ በርዕስዐችን፡ [ሕዝብዓዊ እንቅስቃሴ – ዐማራዊ ቅኔ] ዙሪያ በ ማዉጠንጠን፡ መተጋገዝን ከ’ሚጠይቁ የ–ህይወት ተሞክሮዎችዐችን፥ የ ማኅበረሰብዓዊ እና የ ህብረ–ማኅበረሰብዓዊ ኑሮ ተፈጥሮዓዊ ሰዉዓዊ መለጫዎች መኻከል፡ አንዱ እና ክሪቲካል መስተጋብር መኾንዑን ጠቅሰን – የ ዐማራ ማኅበረሰብ  ያ’ለ–ዕዳው በ ጠላትዕነት ተፈርጆ፡ የ–ድርሻውን ጉልህ አስተዋፅዖ በ መክፈል፡ የ–ፈጠራት ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዳይኖር እና እንድይጠፋ፡ የ–ተቀናጀ ኤትኖ–ሪሊጀስ–ካልቸራል–ኢክናሚክ ጄኖሳይድ እየተፈፀመበት ያ’ለ ማኅበረሰብ ኾኖ እ’ያ እንኳን፥ በ–ኢትዮጵያ እና በ–ኢትዮጵያዊዕነትዑ እምአይደራደር፡ በ ግብረ–ገብዕነት የትዐነፀ እና ቅኔ–ማኅበረሰብ ምኾንዑን፡ ዕንመሰክራለን።

ከዚያም፤ ዛሬ–ላይ ቆመን፡ ስለ ዐማራ [ፋኖ] አለማንሳት፡ ግዙፍ ግድፈት ስለ’ሚኾን፥ የ ዐማራ [ፋኖ]፡ በ ሰላም ቀን፡ ሁለንተናዊ ተፈጥሯዊ ታሪክዓዊ ትስስር ቁርኝት ያ’ው፡ የ ዐማራ ማኅበረሰብ ኢንተግራል ንጥረ–ነገር፥ በ ክፉ ቀን ደሞ፡ በ–ዱር በ–ገደልዑ ተሰማርቶ፡ [የ–ተከዳ፣ የ–ተጎሳቆለ፣ የ–ተከፋ] ወገንዖችዑን እና ኢትዮጵያን፥ በ ቅንዕነት በ በጎ ፈቃደኛዕነት እምይታደግ፡ የ–ሕዝብ እና የ–ሃገር የ–ቁርጥ–ቀን፡ አለኝታችን ምኾንዑን – በ ኩራት እናስገነዝባለን።

አካሄድዐችን ላይ ስንደርስ፤ በ ትህነግ እና ዖዴፓ–ዖነግ ዕኩይ ጥምረት፡ በ ዐማራ ማኅበረሰብዐችን ላይ እየተፈፀመ ያ’ው የ ግፍ–ግፍ፡ ኢ–ሞራል፣ ኢ–ምክንያትዓዊ፣ ኢ–ፍትህዓዊ እና ባዕድዓዊ ጦርዕነት በ ምኾንዑ፥ አምርረን እ’ምንፀየፈው እና እ’ምናወግዘው ምኾንዑን፡ ባ’ፅንዖት እንነግራችኋለን።

ለ–ማጠቃለልም፤ የ ዐማራ ሕዝብዓዊ  እንቅስቃሴ፡ ከ ዘመንዐት አቤቱታ፣ ተማፅኖ፣ ትዕግስት እና ቻይዕነት በኋላ – [ሰሚም ኾነ አራጭ ሲያጣ፡] ራሱን ከ ጥፋት ለ–መታደግ፡ ተገድዶ የ–ገባበት፡ ተፈጥሮዓዊ ሰዉዓዊ መብትዑ ምኾንዑን እናስታዉሳችኋለን። አለኝታዕነቱም፤ ለ ዐማራ ማኅበረሰብ ብቻ ሳይኾን፥ ለ መው ኢትዮጵያዊ ህብረ–ማኅበረሰብ ምኾንዑንም ጭምር። በ መጨረሻም፤ መሠረትዓዊ እና ቀዳሚው ግብዐችን፡ ኢትዮጵያዊያን ሁልዐችንም፡ አምርረን በ–መነሳት፡ የ ጎሣ–ፖሊቲካን እና ኤትኒክ ፌደራሊዝምዑን በ–ማፈራረስ – ኢትዮጵያዊ የ–ሽግግር መንግሥት ምስረታን ሂደት መጀመር፣ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ህገ–መንግሥት መቅረፅ እና ኢትዮጵያዊ ሕዝብዓዊ መንግሥት መመሥረት ምኾንዑ ላይ፡ ብዥታ እንድአይኖር እይአስጠነቀቅን – የ መስከረም ጦማርዐችንን እንቋጫለን።

ሙሉውን ለማንበብ፤ የ አዳራሽ ብሏግ – መስከረም 2016 ዓ.ም ‘ን ይጠቀሙ።

እንአመሰግን አን።